የአርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ የፀረ ሙስናና ሥነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለጫሞ፣ ዓባያና ሳውላ ካምፓሶች አዲስ ገቢ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዲስፕሊን መመሪያ ላይ ከጥር 25 - የካቲት 02/2016 ዓ/ም የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ሥልጠናው በሥነ ምግባር ጽንሰ ሃሳብ፣ የሥነ ምግባር መርሆዎች፣ የሥነ ምግባር ግድፈቶችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ዲሲፕሊን መመሪያ ላይ ያተኮረ ሲሆን ዓላማውም አዲስ ገቢ ተማሪዎች መመሪያውን በሚገባ ተረድተው በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተግባራዊ እንዲያደርጉት ግንዛቤ መፍጠር ነው፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት