በ‹‹Computing and Software Engineering›› ፋከልቲ ለተመደቡ አዲስ የ2 ዓመት ተማሪዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበልና የ‹‹Computing and Software Engineering Club/ CaSE Club/ ትውውቅ መርሃ ግብር የካቲት 13/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የፋከልቲው ዲን መ/ር ጌታሁን ትዕግሥቱ እንደገለጹት ተማሪዎቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት የፋከልቲ መረጣ ያደረጉ ሲሆን በምርጫቸው መሠረት በፋከልቲው ባሉ ሦስት የትምህርት ፕሮግራሞች ለተመደቡ ተማሪዎች የአቀባበል ፕሮግራሙ ተዘጋጅቷል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሠርተው ዐውደ ርእይ የሚያቀርቡበትና አዳዲስ ሃሳቦችን የሚያስተዋውቁበት ‹‹CaSE Club›› በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየ በመሆኑ ክለቡን ዳግም ለማስጀመር ትውውቅ ተደርጓል፡፡

የፋከልቲው መምህራን ዶ/ር መሳይ ሳሙኤልና ዶ/ር መሐመድ አበበ ለተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልእክት ዘመኑ የፉክክር እንደመሆኑ መጪውን ዲጂታል ዓለም የሚመጥን የፈጠራ ሃሳብ ለማመንጨት ያላቸውን ዕምቅ ኃይል በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ፍላጎታቸውን መሠረት አድርገው ለምርምርና ለፈጠራ ሥራ ቢነሳሱ ከፋከልቲው የተለያዩ መረጃዎችንና ድጋፎችን እንደሚያገኙ ገልጸዋል፡፡

የ‹‹CaSE Club›› ፕሬዝደንት ተማሪ ፍራኦል ጎሳ በክለቡ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎች ተባብረው የመሥራት ልምድ እንደሚያካብቱ ገልጾ የትምህርት መስኩን አስመልክቶ ዕውቀትና ልምድ የሚጋሩበት፣ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያገኙበት እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ጋር የሚገናኙበት ነው ብሏል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት