የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከኮሌጁ የተለያዩ ት/ክፍሎች ለተወጣጡ መምህራን እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ለመጡ ባለሙያዎች ‹‹Statistical Data Management and Analysis›› በሚል ርእስ የምርምር ሥራ ደጋፊ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከግንቦት 14-17/2016 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታ ጋልቻ በኮሌጅ ደረጃ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንደሚሰጡ አስታውሰው የምርምር ሥራ ደጋፊ ሶፍትዌሮች ሥልጠና በምርምር ዘርፍ የመምህራንና የተመራማሪዎችን አቅም ለማገንባት የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኮሌጁ የምርምር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስጉን ሸዋንግዛው በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በኮሌጁ የ‹‹GIS››፣ ‹‹Systematic Review Grant Writing›› እና ሌሎችም ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ጠቅሰው ‹‹Statistical Data Management and Analysis›› በሚል ርእስ የተሰጠው ሥልጠና በምርምር ዘርፍ የመምህራንን አቅም ለማሳደግ፣ ለተማሪዎች የተሻለ ዕውቀት ለማስተላለፍና ለተገልጋዩ ኅብረተሰብ በምርምር የታገዘ ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማስቻል ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የስታትስቲክስ ት/ክፍል መምህርና ተመራማሪ አቶ ደፋሩ ደበበ ‹‹Statistical Data Analysis Using SPSS›› እና ‹‹Introduction to STATA Graphics Using STATA and Statistical Tests›› በሚሉ ይዘቶች ሥልጠና የሰጡ ሲሆን ሶፍትዌሮቹ በምርምር ወቅት መረጃን በቀላል መንገድ ለመያዝና ለመጠቀም እንዲሁም ሳይንሳዊ ውጤቶችን ለማውጣት የሚያገልግሉ መሆኑን አሠልጣኙ ገልጸዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት