በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል አዘጋጅነት በሁሉም ካምፓስ ተማሪዎች መካከል ሲደረግ የቆየው የ2015 ዓ/ም 2ኛ ዙር የንግድ ሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር ሰኔ 16/ 2015 ዓ/ም ተጠናቋል፡፡ በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ስድስት የቢዝነስ ፈጠራ ሃሳቦች ቀርበው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ገንዘብ ሽልማት እንዲሁም ለቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡ የተሻሻለ የእንጀራ መጋገሪያ ማሽን፣ ዘመናዊ ጡብ ማምረቻ፣ ከአፈር ውጭ ውሃን በመጠቀም የጓሮ አትክልቶችን ማምረትና ከሙዝ ግንድ ወረቀት ማምረት ከቀረቡ የፈጠራ ሥራ ሃሳቦች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ከጋሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን  ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር ከዞኑ  14 ወረዳዎች፣ ስድስት የከተማ አስተዳደሮችና አምስት የግል ማኅበራት ለተወጣጡ የICT እና የቢሮ ማሽን ጥገና ባለሙያዎች ከሰኔ 12- 16/2015 ዓ/ም የቢሮ ማሽን ጥገና ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎክን የመጻሕፍትና መረጃ ማዕከል ከበጎ አድራጎት ማዕከል ጋር በመተባበር  በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚገኙ ልማት እና አርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ለማረሚያ ብሩህ ተስፋ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ለሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት ከተለያዩ አካላት በልገሳ ያገኟቸውን የመማሪያ ማጣቀሻ መጻሕፍት እና አልባሳት ድጋፍ ግንቦት 22/2015 ዓ/ም  አበርክተዋል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

Arba Minch University Law School students Team wins International Committee of Red Cross, ICRC, National Moot Court Competition on International Humanitarian Law held in Addis Ababa from May 29-30/2023. Click here to see the Pictures!

በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኮምፒውቲንግና ሶፍትዌር ኢንጂነርንግ ፋከልቲ በ “Computing and Information Technology” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል  ሰኔ 02/2015 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ ከ8፡30 ጀምሮ  የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናዉ ግቢ መግቢያ አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ ያቀርባል፡፡