- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትኩረት የሚሹ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ሥልጠናና ምርምር ማዕከል ከጤና ሚኒስቴርና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር በተዘነጉ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ሀገር አቀፍ ፕሮግራም የመረጃ ጥራት ምዘና ጥናት ለማድረግ በተደረሰ ስምምነት መሠረት በመረጃ ሰብሳቢነት ለተመረጡ የኮሌጁ መምህራን ጥር 16/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የተዘነጉ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ሀገር አቀፍ ፕሮግራም የመረጃ ጥራት ምዘና ጥናት ሊደረግ ነው
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የዩኒቨርሲቲውን የ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ጥር 12/2015 ዓ/ም ገምግሟል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ተገመገመ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደበበ ኃይለገብርኤል የሕግ ቢሮ ጋር በመተባበር «የብሔር ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ የተሻለ አማራጭ ነው ወይስ ስጋት?» እንዲሁም «በፖለቲካና በኢኮኖሚ የመልካም አስተዳደር ስኬትን ለማረጋገጥ የራስን ዕድል በራስ መወሰን ትክክለኛ አማራጭ ነው ወይስ አይደለም?» በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥር 14/2015 ዓ/ም የክርክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
ከጀርመን ልማት ባንክ በተገኘ 25 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የጫሞ ሐይቅ ተፋሰስን ወደነበረበት ለመመለስ በቅርቡ ሥራ የሚጀምረው ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን ከጋሞና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ከደራሼ፣ ቡርጂና አማሮ ልዩ ወረዳዎች የተወጣጡ አስተዳዳሪዎችን እና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኃላፊዎችን ያካተተ የአመራሮች የጋራ መድረክ ጥር 10/2015 ዓ/ም በይፋ ተመሥርቷል፡፡ በዕለቱ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴም የአመራር መድረኩ ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የጫሞ ሐይቅ ተፋሰስን ወደነበረበት ለመመለስ ለሚሠራው ፕሮጀክት የአመራሮች የጋራ መድረክ ተመሠረተ
- Details
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን ሰብሳቢ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር እያሱ ኤሊያስ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ተመራማሪዎች ጋር በተለያዩ የምርምር ግኝቶች፣ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችና በትብብር መሥራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ጥር 10/2015 ውይይት አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንሰትን የተቋሙ ብራንድ ለማድረግ እንዲሠራ የቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሳሰቡ