በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነጽሑፍ ት/ክፍል በ‹‹English Language Teaching (ELT)›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ጋሻው ተፈራ ጥር 24/2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የመመረቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያቀርባል፡፡  

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹Regional Consultative Workshop on Constraints and Opportunities of Sorghum Production in the Southern Ethiopia›› በሚል ርዕስ አርብቶ አደሩን ማኅበረሰብ የማስተዋወቅ፣ የማላመድና የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጡ የማገዝ ፕሮጀክት መክፈቻ ወርክሾፕ ጥር 13/2015 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

 Arba Minch Institute of Technology is to host the 1st Joint Research Symposium in Hybrid mode on 30 & 31 of January 2023. See more photos

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትኩረት የሚሹ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ሥልጠናና ምርምር ማዕከል ከጤና ሚኒስቴርና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር በተዘነጉ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ሀገር አቀፍ ፕሮግራም የመረጃ ጥራት ምዘና ጥናት ለማድረግ በተደረሰ ስምምነት መሠረት በመረጃ ሰብሳቢነት ለተመረጡ የኮሌጁ መምህራን ጥር 16/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የዩኒቨርሲቲውን የ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ጥር 12/2015 ዓ/ም ገምግሟል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ