የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክቶሬት 10ውን ዓመታዊ የምርምር ግምገማ ዎርክሾፕ ከጥር 19 -20/2015 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ የብዝሃ ሕይወት ጥናት ኢንስቲትዩት፣ አሜሪካ ሀገር ከሚገኘው ‹‹Alabaster International››፣ ከኬንያው ጆሞ ኬንያታ የግብርናና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና ከ‹‹Girl Child Network›› ጋር እንሰትን በኢትዮጵያና በምሥራቅ አፍሪካ ለማስታዋወቅና የምግብ ዋስትና መፍትሔ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ፕሮጀክት ቀርጸው ለመሥራት ቅድመ ዝግጅቶችን እያጠናቀቁ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ተቋማቱ በቅርቡ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ወደ ሥራ የሚገቡ ሲሆን ከተቋማቱ የመጡ የሥራ ኃላፊዎች በመስኩ የተሠሩ የምርምር ሥራዎችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከዩኒቨርሲቲው አመራሮችና የዘርፉ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን ከጥር 17-19/2015 ዓ/ም የመስክ ምልከታና የጋራ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

Arba Minch University Senate promoted Dr. Muluneh Lemma Woldesemayat, an assistant professor and researcher in the faculty of Electrical and Computer Engineering, to an Associate Professorship Academic Rank on January 21, 2023.

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነጽሑፍ ት/ክፍል በ‹‹English Language Teaching (ELT)›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር  ተፈሪ ሀቱዬ ጥር 25/2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የመመረቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያቀርባል፡፡