- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞና ኮንሶ ዞኖች ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ከኮሌጆቹ ለተወጣጡ መምህራን ‹‹Advance Solid Work››፣ ‹‹Basic Solid Work›› እና ‹‹ArchiCAD›› በተሰኙ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከታኅሣሥ 10-14/2015 ዓ/ም የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ለተወጣጡ መርማሪ ፖሊሶች በፎረሲንክ ወንጀል ምርመራ ዘዴ እና የፎረንሲክ ማስረጃ ዝግጅት ዙሪያ ከታኅሣሥ 12-14/ 2015 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጋሞ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን ለሚገኙ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ከታኅሣሥ 13-14/2015 ዓ/ም የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ9ኛ ጊዜ በተከበረው የኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት ላይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ወክላ የቀረበችው የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል 4ኛ ዓመት ተማሪ ሱመያ ፌቲ ባቀረበችው የቢዝነስ ሃሳብ 2ኛ በመውጣት ኅዳር 25/2015 ዓ/ም ከሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር 260 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናለች፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በሀገር አቀፍ የኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት ዩኒቨርሲቲውን የወከለችው ተማሪ በ2ኛነት አሸነፈች
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ማእከል ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ በሀገራችን ለ30ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን ከ6ቱም ካምፓስ ከመጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጋር ታኅሣሥ 9/2015 ዓ/ም ተከብሯል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡