አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆን ከወዲሁ ይመኛል፡፡

መልካም በዓል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ከምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በእንቦጭ አረምና በአኩሪ አተር ጠቀሜታ ዙሪያ ከኢንዶኔዥያ በመጡ የመስኩ ባለሙያዎች ለኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች መስከረም 12/2015 ዓ/ም የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቤልጂየም ሀገር 5 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር የሚሠራው “AMU-IUC – Arba Minch University – Institutional University Cooperation”  ፕሮግራም 2 ዙር የኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎና በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር ስቴፋን ቲጂስ/Stefaan Thijis/ በተገኙበት መስከረም 11/2015 ዓ/ም በይፋ ተጀምሯል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አቶ ሙሉነህ መንገሻ ከአባታቸው ከአቶ መንገሻ ቃንኤ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዓለሚቱ በላቸው በቀድሞ በሰሜን ኦሞ ዞን በጋሞ አውራጃ በቁጫ ወረዳ መስከረም 12/1958 ዓ.ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ በጎፋ ወረዳ በገልጣ ከተማ  1- 6 ክፍል በገሪማ 1 ደረጃ ት/ቤት፣ ከ7- 8 ክፍል በአርባ ምንጭ ከተማ በኩልፎ ሙሉ 1 ደረጃ ት/ቤት እና ከ9- 10 ክፍል  የ2 ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ  2 ደረጃ  ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡