- Details
ወ/ሮ መርታን መርዕድ ከአባታቸው ከአቶ መርዕድ ዱለቻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አየለች ቡሩኮ በአርባ ምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ ጳጉሜ 3/1978 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን (ከ1ኛ - 6ኛ) ክፍል በዓለም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በኩራዝ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጂንካ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን በ1996 ዓ.ም ሚዛን ቴፒ ግብርና ኮሌጅ በመግባት በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ትምህርት በ1998 ዓ/ም በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለሁሉም ካምፓሶች ለተመራቂ ተማሪዎች ወደ ሥራ ዓለም ሲገቡ ሊገጥሟቸው የሚችሉ የብልሹ አሠራር ችግሮችን የመከላከል ግንዛቤን ለማዳበር ከመስከረም 5-6/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮች በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት፣ በሳምንት መጨረሻ እና በተከታታይና ርቀት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ የ35ኛው ባች 2ኛ ዙር 1,200 ተማሪዎችን መስከረም 12/2015 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 84ቱ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን ከአጠቃላይ ምሩቃንም 387ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪና በ2ኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ያሠለጠናቸውን የ35ኛ ባች ተማሪዎች ለ2ኛ ጊዜ አስመረቀ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ትምህርትና ሥነ ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት በሦስት የ2ኛ ዲግሪ የትምህርት መርሃ ግብሮች ላይ መስከረም 04/2015 ዓ/ም የሥርዓተ ትምህርት የውጭ ግምገማ አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የሥነ ትምህርትና ሥነ ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የ2ኛ ዲግሪ መርሃ ግብር የሥርዓተ ትምህርት የውጭ ግምገማ አካሄደ