ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሮችና የሲስተም አስተዳደር ባለሙያዎች ‹‹Federated Identity System and Educational Roaming›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 24-26/2015 ዓ/ም  በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ19/12/2ዐ14 ዓ.ም በምክትል ፕሬዝደንትነት ማዕረግ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር አወዳድሮ ለመሰየም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛውን መስፈርት በማሟላት በመመሪያው መሠረት ከስር በስም የተገለጻችሁ ተወዳዳሪዎች ኅዳር 6/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለሚከናወነው ፓናል ኢንተርቪው እና ስትራቴጅክ ዕቅድ ገለፃ የተመረጣችሁ በመሆኑ በስም ዝርዝሩ ቅደም ተከተል መሠረት በተከታታይ ስለምታቀርቡ በተጠቀሰው ቀን በአዲሱ የስብሰባ አዳራሽ በሰዓቱ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ19/12/2ዐ14 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝደንት አወዳድሮ ለመሰየም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛውን መስፈርት በማሟላት በመመሪያው መሠረት ከስር በስም የተገለጻችሁ ተወዳዳሪዎች ኅዳር 5/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለሚከናወነው ፓናል ኢንተርቪው እና ስትራቴጅክ ዕቅድ ገለፃ የተመረጣችሁ በመሆኑ በስም ዝርዝሩ ቅደም ተከተል መሠረት በተከታታይ ስለምታቀርቡ በተጠቀሰው ቀን በአዲሱ የስብሰባ አዳራሽ በሰዓቱ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡

 

የአፍሪካ ወጣቶች ወር በአፍሪካ ደረጃ “Breaking the Barriers to Meaningful Youth Participation and Inclusion in Advocacy” በሚል መሪ ቃል ከኖቨምበር 01/2022 እ.ኤ.አ ጀምሮ እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በሀገራችን ደግሞ በነገው ዕለት ከጧቱ 02፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ በሚገኘው ትልቁ አዳራሽ “ንቁ የወጣቶች ተሳትፎና ተካታችነት ለስብዕና ልማት” በሚል መሪ ቃል ለ16 ጊዜ  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የወጣቱን ግንዛቤ፣ ተሳትፎና ስብዕና በሚገነባ መልኩ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች የሚከበር ይሆናል፡፡  በልዩ ትኩረት በትምህርትና ስብዕና ልማት፣ ወጣትና ሥራ ፈጣሪነት፣ የወጣቶች ተዋልዶ ጤናና ስብዕና ልማት እና አደንዛዥ ዕጽ በወጣቶች ስብዕና ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖና ሌሎችም የውይይት ጉዳዮች የተካተቱበት ይሆናል፡፡

Arba Minch University congratulates and wishes all the best to Pal Mai Deng, AMU post graduate Masters of Business Administration (MBA) 1st year foreign student, on his current government appointment as the Minister for Water Resources and Irrigation in the Republic of South Sudan. He is one of the foreign students who got Master’s Degree Scholarship in MBA program and joined Arba Minch University in the year 2021. To See more Pictures Click here.