በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና  ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማ/ጽ/ቤት በአርባ ምንጭ ከተማ እና አጎራባች ቀበሌያት በፈሳሽና ደረቅ ሳሙና አዘገጃጀት ሥራ ላይ ለተደራጁ 6 ማኅበራት ለሥራው የሚያግዙ የአላቂና ቋሚ ቁሳቁስ ድጋፍ ጥቅምት 17/2015 ዓ/ም አድርጓል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ትምህርት ክፍል «Bio Diversity Conservation and Management» ትምህርት ፕሮግራም ላላፉት 5 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት እጩ ዶ/ር ተመስገን ዲንጋሞ የምርምር ሥራቸውን ጥቅምት 21/2015 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርበው ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ማዕከል ማስ/ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከሆስፒታሉ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች በወባ በሽታ ምርመራና ሕክምና አሰጣጥ አዳዲስ አሠራሮች ዙሪያ ከጥቅምት 18-19/2015 ዓ/ም የሁለት ቀናት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ በ2014 በጀት ዓመት ያካሄደውን የማዕድን ሀብት አለኝታ ጥናት ውጤት የክልሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ማዕድንና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን እንዲሁም የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ጥቅምት 17/2014 ዓ.ም ይፋ አድርጓል። ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

መ/ር ወንዱ ዳባ ከአባታቸው ከአቶ ዳባ ሞጆ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ደስታ አመኑ በቀድሞ ሰሜን ኦሞ ዞን ጋርዱላ አውራጃ በጊዶሌ ወረዳ ጥር 7/1965 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

መ/ር ወንዱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ክ/ሀገር በጊዶሌ ወረዳ ጊዶሌ መለስተኛ 1 ደረጃ ት/ቤት፣ እንዲሁም የ2 ደረጃ  ትምህርታቸውን በጊዶሌ 2 ደረጃ  ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡