በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጁ ሰባት የፈተና መስጫ መዕከላት በሁለት ዙሮች ለማኅበራዊና ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በሠላምና በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማ/ጉድ/ ዳይሬክቶሬት በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ በሻማ ቀበሌ እያስገነባ የሚገኘውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የሥራ አፈፃፀም በዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝደንት የተመራ የልዑካን ቡድን ጥቅምት 1/2015 ዓ/ም የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብሮች አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ፈተና መስጠቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሠረት ከተወዳዳሪዎች መካከል በውጤታቸው መሠረት ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲገቡ የተመረጡ ዕጩዎች የቅበላና ምዝገባ ቀን በቅርብ ቀን ውስጥ የምንገልጽ መሆኑን እየሳወቅን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ የሚገቡ ነገሮችን በቅድሚያ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-

የ2014 ዓ/ም የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 11/2015 ዓ/ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም ምክንያት የዩኒቨርሲቲው የተወሰኑ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ብቻ ልዩ የመግቢያ ባጅ ተሰጥቶ ወደ ግቢ የሚገቡ ሲሆን ሌሎች ሠራተኞች ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 12/2015 ዓ/ም ድረስ ቤታችሁ ሆናችሁ ሥራዎችን እንድታከናውኑ ያሳውቃል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተዘነጉ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ከጤና ሚኒስቴር ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት በሚኒስቴሩ አማካኝነት የተደረገን የመድኃኒት ስርጭት ሽፋን ማረጋገጫ ዳሰሳ ጥናት ለማከናወን በአራት ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር ሥራውን ለሚያከናውኑ መረጃ ሰብሳቢዎች ከመስከረም 18-19/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ