ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝደንት እና በምክትል ኘሬዝደንት ማዕረግ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ውድድር የቀረቡ ተወዳዳሪዎች የስትራቴጅክ ዕቅድ ገለፃ የሚያቀርቡት፤

 

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝደንት ለመምረጥ በ19/12/2014 ዓ.ም በወጣው የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ መሠረት ከተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛውን መስፈርት በማሟላት የቀረቡ ተወዳዳሪዎች በመመሪያው መሠረት የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት እና ነባር መምህራን ወይም ተመራማሪዎች በተገኙበት የስትራቴጅክ ዕቅድ ገለጻ የሚደረግ ስለሆነ የኢንስቲትዩቶች፣ የኮሌጆች እና የት/ቤቶች ዲኖችና ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች እንዲሁም የአስተዳደር ዳይሬክተሮች ከየዘርፋችሁ የካውንስል አባላት እና ከየትምህርት ክፍሉ አንድ አንድ ነባር/Senior/ መምህር ወይም ተመራማሪ ይዛችሁ በ5/03/2015 ዓ.ም 2፡3ዐ በዋናው ግቢ መግቢያ በር አካባቢ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርገው የተዘጋጁ 35 ንድፈ-ሃሳቦች ቀርበው ከጥቅምት 24-25/2015 ዓ/ም ግምገማ ተካሂዶባቸዋል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ከዩኒቨርሲቲው ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር  ለዩኒቨርሲቲው  ካውንስል አባላት ግምገማዊ የሥልጠና መድረክ ጥቅምት 22/2015 ዓ/ም አዘጋጅቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል በ“Operation Research” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ ፀጋዬ ነገ ቅዳሜ ኅዳር 03/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓባያ ካምፓስ በፒ.ኤች.ዲ. አዳራሽ እንዲሁም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በማኔጅመንት ት/ክፍል በ“Marketing Management” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ስንታየሁ አሰፋ  ረቡዕ ኅዳር 7/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመመረቂያ ፅሑፎቻቸውን በማቅረብ የሚያስገመግሙ ይሆናል፡፡ በመድረኩም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች ይገኙበታል፡፡