በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ባዮሎጂ ት/ክፍል በ‹‹Infectious Disease›› የ3ኛ እንዲሁም በ‹‹Medical Entomology and Vector Control›› የ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በ‹‹NORHED-SENUPH II›› ፕሮጀክት ድጋፍ ለሚከታተሉ ተማሪዎች በሞሎኪዩላር ባዮሎጂ ቤተ-ሙከራ የሚገኙ የተለያዩ የ‹‹Polymerase Chain Reaction (PCR)›› ማሽኖችን ለምርምር ሥራዎች በመጠቀም ዙሪያ ለ3 ሳምንታት የቆየ ሥልጠና ከሐምሌ 25/2014 ዓ/ም ጀምሮ ተሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዓለም አቀፍ የጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት (GIS) ሶፍትዌር፣ የዌብ ጂ.አይ.ኤስና የጂኦዳታቤዝ አስተዳደር መተግበሪያዎች አቅራቢ ድርጅት የሆነው ‹‹Environmental Systems Research Institute (ESRI)›› በአሜሪካን ሀገር ሳንዲያጎ-ካሊፎርኒያ ከሐምሌ 01-09/2014 ዓ/ም ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ‹‹ESRI User Conference›› እና ‹‹Education Summit›› ላይ የተገኘው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር ኢትዮጵያን ወክሎ ለዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግብ ስኬት የሚረዱ መረጃዎችን እንዲያሰባስብ ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

“ኢትዮጵያን እናልብሳት!” እና “Green Legacy; Green Campus!” በሚሉ መሪ ቃሎች በ4ው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ በቤሬ ተፋሰስና በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ከነሐሴ 12/2014 ዓ/ም ጀምሮ 25,000 ችግኞችን እንደሚተክል ተገልጿል፡፡

“TAY Authorized Accountants and Auditors” የተሰኘ ድርጅት ነጸ የ3 ወራት የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ያዘጋጀ ስለሆነ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ እና አካውንቲንግና ፋይናንስ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቃችሁ ምሩቃን ከዚህ ቀጥሎ ባለው ማስፈንጠሪያ መመዝገብ የሚትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማስፈንጠሪያው - https://www.tayauditing.com/internship-programs/  

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እስከ አሁን ባለው አፈጻጸም የሦስቱም ዙሮች የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቆ 2ው ተርባይን ኃይል ማመንጨት በመጀመሩ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ለመግለጽ ይወዳል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የምትኖሩ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ባለ ድልና ባለ ዕድል ትውልድ ለመሆን አበቃን፡፡