የዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ አማርኛ ት/ክፍል ጋር በመተባበር ለአርባ ምንጭ ከተማ ማረሚያ ተቋም፣ ለጨንቻ ከተማ ወጣቶች ቤተ-መጻሕፍትና በጨንቻ ለሚገኘው ሆሎኦና ላካ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ታኅሣሥ 6/2014 ዓ.ም የመጻሕፍት ድጋፍ አድርጓል፡፡ መጻሕፍቱ በቁጥር 433 ሲሆኑ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ የተለያዩ ጀግኖች ታሪክ፣ ልብወለዶች፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ፣ የቋንቋ እና የትምህርት ማጣቀሻዎችን የሚያካትቱ ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ት/ክፍል ከዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት እና ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስትሮኖሚና አስትሮ ፊዚክስ ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ታኅሣሥ 04/2014 ዓ/ም ሥልጠናዊ ወርክሾፕ አዘጋጅቷል፡፡ በወርክሾፑ ማጠናቀቂያም በኢንስቲትዩቱ እንደ ሀገር ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው በጉጌ ተራራ በመገኘት የጣቢያ ምልከታ ተከናውኗል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን፣ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችንና የዘማች ቤተሰቦችን ለመደገፍ የ2ኛ ደረጃ መምህራንንና ተማሪዎችን በማሳተፍ የተጀመረው ሀገራዊ የድጋፍ ዘመቻ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዩኒቨርሲቲው ኮሚዩኒቲ ት/ቤት ታኅሣሥ 01/2014 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የዩኒቨርሲቲያችንን ማኅበረሰብ የሀገራችን ብሔራዊ ጉዳዮችን በሚያገኙት ሚዲያ ሁሉ (በዋነኛነት በሶሻል ሚዲያ ላይ) እንዲያስተጋቡና እንዲያስተዋውቁ ማስተባበር ዋና ተግባሩ ነው፡፡ ለዚህም ተግባር ይረዳ ዘንድ የሀገራችንን ብሔራዊ አጀንዳዎች ለዜጎች በስፋት ማስተዋወቅና ግንዛቤ ማስጨበጥ በጣም አስፈላጊና ቀዳሚ ሥራ ነው፡፡

ዓለም አቀፍ የነጭ ሪባን ቀን ‹‹በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃቶችን በመከላከልና በማስቆም አጋርነታችንን እናሳይ!›› በሚል መሪ ቃል ሳውላ ካምፓስን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ካምፓሶች ከኅዳር 16/2014 ዓ/ም ጀምሮ ተከብሯል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ