አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀጥሎ በተገለፁት ክፍት የሥራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን  አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ Click here to download the vacancy announcement.

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2010 ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመለከታችሁ ተወዳዳሪዎችን የማጣራት ሥራ በማጠናቀቅ ለፅሑፍ ፈተና ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በቀድሞው ማስታወቂያ 2.75 የመመረቂያ ነጥብ ለወንዶችና 2.5 የመመረቂያ ነጥብ ለሴቶች ኑሯችሁ ለሌክቸራርነት እንዲሁም 2.5 እና ከዚያ በላይ ኑሯችሁ ለቴክኒካል አሲስታንትነት አመልክታችሁ ለፅሁፍ ፈተና ያልተጋበዛችሁ (Not Selected) የሆናችሁትን እንዳላችሁ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በየዘርፉ የተጠቀሰውን አነስተኛ መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ የፅሁፍ ፈተናውን ሐምሌ 26፣ 2010 ዓ/ም በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመገኘት እንድትወስዱ ማሻሻያ የተደረገ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2010 ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመለከታችሁ  ተወዳዳሪዎችን የማጣራት ሥራ የተጠናቀቀ ስለሆነ ለፈተና ያለፋችሁ ተወዳዳሪዎች ለፅሑፍ ፈተና ሐምሌ 26፣ 2010 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንድትገኙ ያሳስባል፡፡

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት ለ2011 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሣምንት መጨረሻ መርሐ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቶችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ Click here to download the full information and the Application form.

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል በ2010 ዓ/ም ለተመረቁ 240 የአካውንቲንግና ፋይናንስ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች /IFRS/ ላይ ከሰኔ 25-29/2010 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 5 ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::