የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር በፎረንሲክ ወንጀል ምርመራ ዘዴና ማስረጃ አያያዝ ዙሪያ ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ 36 የፎረንሲክ ምርመራ ፖሊስ መኮንኖች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ለተወጣጡ የጥበቃ ሠራተኞች ከታኅሣሥ 7-9/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የ2014 ዓ/ም የ1ኛ ተርም የአዲስ ተመዝጋቢዎች የ1ኛ ሴሚስተር የርቀት ትምህርት የምዝገባ፣ የቲቶሪያልና የፈተና መርሃ-ግብር ከዚህ ቀጥሎ ባለው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በተመዘገባችሁበት ማዕከል የሚከናወን መሆኑን እየገለጽን በጊዜ ሠሌዳዉ መመዝገብ ያልቻለ ተማሪ በቅጣት መመዝገብ የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባዮ ቴክኖሎጂ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አዲሱ ፈቃዱ በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በተደረገ ሀገር አቀፍ የምግብ ፈጠራ ሥራዎች ውድድር 1ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ውድድሩ ከኅዳር 29 - ታኅሣሥ 1/2014 ዓ/ም ከተካሄደው ሀገር አቀፍ የሥነ-ምግብ ምርምር ኮንፍረንስ ጋር ተያይዞ የተደረገ ሲሆን በውድድሩ ከ11 ተቋማት የተወጣጡ የፈጠራ ሰዎች ተካፍለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ አማርኛ ት/ክፍል ጋር በመተባበር ለአርባ ምንጭ ከተማ ማረሚያ ተቋም፣ ለጨንቻ ከተማ ወጣቶች ቤተ-መጻሕፍትና በጨንቻ ለሚገኘው ሆሎኦና ላካ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ታኅሣሥ 6/2014 ዓ.ም የመጻሕፍት ድጋፍ አድርጓል፡፡ መጻሕፍቱ በቁጥር 433 ሲሆኑ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ የተለያዩ ጀግኖች ታሪክ፣ ልብወለዶች፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ፣ የቋንቋ እና የትምህርት ማጣቀሻዎችን የሚያካትቱ ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ት/ክፍል ከዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት እና ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስትሮኖሚና አስትሮ ፊዚክስ ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ታኅሣሥ 04/2014 ዓ/ም ሥልጠናዊ ወርክሾፕ አዘጋጅቷል፡፡ በወርክሾፑ ማጠናቀቂያም በኢንስቲትዩቱ እንደ ሀገር ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው በጉጌ ተራራ በመገኘት የጣቢያ ምልከታ ተከናውኗል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ