- Details
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞች፣ የዘርፉ የ10 ዓመት የልማት ፍኖተ ካርታና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ዙሪያ እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠናዊ ውይይት በዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች እየተካሄደ ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በዩኒቨርሲቲው 2ኛው ዙር የከፍተኛ ትምህርት ፐሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና የ10 ዓመት የልማት ፍኖታ ካርታ ሥልጠና እየተካሄደ ነው
- Details
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ110ኛ በሀገራችን ለ45ኛ ጊዜ የተከበረው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹የሴቶችን መብት የሚያከብር ማኅበረሰብ እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 8/2013 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ተከብሯል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በመክፈቻ ንግግራቸው ሴቶች የኅብረተሰቡ ግማሽ አካል በመሆናቸው በአንድ ሀገር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጉልህ ሚና ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡ በተለያዩ ተፅዕኖዎች ምክንያት የሴቶች ተሳትፎ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር ያነሰ ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ አሁን በደረስንበት የዕድገት ደረጃ በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገራችን በሁሉም መስኮች የሴቶች ተሳትፎ በመጠንና በውጤታማነት ትልቅ ዕድገት እያሳየ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲውን ለሴት ተማሪዎች ምቹ ለማድረግ ሁሉም በትብብር መሥራት እንደሚጠበቅበትም ፕሬዝደንቱ አሳስበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
‹‹የጠራ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድ፣ ፕሮግራሞችና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ግንዛቤና ትግበራ ለኢትዮጵያ ዕደገት፣ ልማትና ብልፅግና›› በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 10/2013 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢና ሳውላ ካምፓስ ከሚገኙ የካውንስል አባላትና ሠራተኞች ጋር የአሠልጣኝነት ሥልጠናዊ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
125ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ‹‹ዓድዋ የኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ዓርማ›› በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ በሰላም ሚኒስቴር አማካኝነት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በመምጣት ለ45 ቀናት በማኅበረሰብ አቀፍ የበጎ አገልግሎት ሥልጠና ላይ የቆዩ ወጣቶች ሽኝትም ተካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የእንሰት ምርት ሂደትን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እየሠራ ያለው ሥራ አበረታችና ሊሰፋ የሚገባው መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ተናገሩ፡፡ በምክር ቤቱ የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በዩኒቨርሲቲውና በኢንስቲትዩቱ በኢኖቬቲቭ እንሰት ፕሮጀክት አማካኝነት እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ከየካቲት 27-28/2013 ዓ/ም በመስክ በመገኘት ምልከታ አድርገዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የእንሰት ምርት ሂደትን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ አበረታች መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ገለጹ