Arba Minch University rolled out a total of 1,475 graduates in its 36th batch 2nd round convocation held at Main Campus Auditorium, on September 23, 2023; 1,348 are undergraduates, 121 are Masters, 3 PGDTs and 3 are PhDs. Click here to see more Photos.

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አውስትራሊያ ሀገር ከሚገኘው ‹‹Menzies School of Health Research›› ከተሰኘ የጤና ምርምር ት/ቤት ጋር በመተባበር በሚያከናውኑት  የጥናት ውጤት ላይ ግምገማዊ ወርክሾፕ መስከረም 8/2016 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ከበደ ገልገሎ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በእንስሳት ሳይንስ ትምህርት ክፍል በእንስሳት ሥነ-ምግብ/Animal Nutrition/ ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ከበደ የ3 ዲግሪ የመመረቂያ ጽሑፉን የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት መስከረም 15/2016 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ  በዋናዉ ግቢ አዲሱ አዳራሽ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መስከረም 10/2016 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ በመጀመሪያ፣ በ2 እና በ3 ዲግሪ በመደበኛው መርሃ ግብር በምኅንድስና፣ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ፣ በግብርና ሳይንስ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነሰብ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከ1,400 በላይ ተማሪዎች እንዲመረቁ አጽድቋል፡፡

ዶ/ር ብሩክ አማረ ስራቴ ከአባታቸው ከአቶ አማረ ስራቴ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አልማዝ አበበ በጋሞ አውራጃ አርባ ምንጭ ከተማ መስከረም 6/1977 ዓ/ም ተወለዱ፡፡