በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ ̋Biotechnology” ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ሳምሶን ትዕዛዙ የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ማጠናቀቂያ የምርምር ሥራውን መስከረም 4/2016 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና እና የስኬት ይሁንላችሁ፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ"Biodiversity Conservation and Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ማቲዎስ አጊዜ የምርምር ሥራውን ነሐሴ 29/2015 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን የፌዴራል የመንግሥት ተቋማትን የግዥ ሥርዓት ለማሻሻልና ለማዘመን  በ“Electronic Government Procurement /eGP” ዙሪያ ለዘርፉ የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቲዎሪና በተግባር የተደገፈ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ከጳጉሜ 2-4 /2015 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ‹‹Biotechnology›› ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሳምሶን ትዕዛዙ  መስከረም 04/2016 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ  የ3 ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዓባያ ካምፓስ በአዲሱ ማኔጅመንት ሕንፃ አዳራሽ ያቀርባል፡፡