በአዲሱ የፌዴራል መንግሥት መዋቅራዊ አደረጃጀት ለውጥ መሠረት በሠራተኞች የድልድል አፈጻጸም መመሪያ ዙሪያ በሁሉም ካምፓስ ለሚገኙ የአስተዳደር ሠራተኞች ከነሐሴ 16-19/2015 ዓ/ም ድረስ ገለጻ ተደርጓል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን ሀገር ከሚገኘው ዓለም አቀፍ ሮትራክት ድርጅት/Rotary Club Bonn International/ እና ሮተሪ ኢትዮጵያ/Rotary Ethiopia/ ጋር በመተባበር ‹‹Environmental Sustainability, Water and Agroforestry with Permaculture for Gircha in Ethiopia›› የተሰኘና ለሦስት ዓመታት የሚቆይ አዲስ የትብብር ፕሮጀክት በቆጎታ ወረዳ ነሐሴ 20/2015 ዓ/ም ይፋ አድርጓል፡፡ በግብርናና ደን፣ አፈርና ውሃ ጥበቃ፣ ንጽሕናው የተጠበቀ የቤት አሠራርና አያያዝ እና የሶላር ፕላንቶች ጥገና ላይ ሥልጠናዎችን መስጠት፣ በማኅበረሰቡ ቤቶች አስተማሪ ፖስተሮችን ማቅረብ እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ውጤቶች ዘላቂነት ትብብሮችን መመሥረት በፕሮጀክቱ ከሚተገበሩ ሥራዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ AMU-IUC ፕሮግራም ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነውና በጤናው ዘርፍ የእናቶችንና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል የሚተገበረው ፕሮጀክት የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምርምር ውጤት የደረሰበትን ደረጃ የማስተዋወቂያ ወርክሾፕ ነሐሴ 18/2015 ዓ/ም ተካዷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር አበራ ሽጉጤ በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ“Water Resource and Irrigation Engineering” ፋካልቲ  በ‹‹Irrigation and Drainage Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር አበራ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፉን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ አዲሱ አዳራሽ ነሐሴ 26/2015 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ  የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በአርባ ምንጭ ከተማ ሲያካሂደው የነበረው ስብሳባ መጠናቀቅ ተከትሎ የስብሳበው ተሳታፊዎች አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ የሚገኘውን የእንሰት፣ የጫሞ ሐይቅን መልሶ የማልማት እና ሌሎች የምርምር ግኝት ውጤቶች የመስክ ምልከታ ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡