ወ/ሮ እታገኝ ጓሉ ከአባታቸው ከአቶ ጓሉ ገብሬ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወጋየሁ ጓሉ በቀድሞ ወሎ ክፍለ ሀገር በወልድያ ከተማ የካቲት 16/1974 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹የምሁራን ሚና ለሀገራዊ መግባባት›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የሥራ ኃላፊዎችና ተማሪዎች በተገኙበት የካቲት 25/2015 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትኩረት የሚሹ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ምርምርና ሥልጠና ማዕከል በደቡብ ኦሞ ዞን በተለይም በሙርሲ አካባቢ የቪሰራል ሌሽማኒያሲስ/Visceral Leishmaniasis/ በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር ማሻቀብን ተከትሎ የምርመራ ናሙና ለሚወስዱ ሐኪሞችና ወረርሽን መከሰት አለመከሰቱን ለማረጋገጥ ዳሰሳ ለሚያካሂዱ ከዞኑ ወረዳዎችና ከጂንካ ከተማ ለተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች የካቲት 25/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ


127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ‹‹ዝክረ ዓድዋ ድል ለብሔራዊ መግባባት›› በሚል መሪ ቃል ያለፈውን ታሪክ በመዘከር፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጸና እና የሀገር ግንባታን በሚያጠናክር መንፈስ የካቲት 23/2015 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial Program/ ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉትን ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በግል ከፍሎ ለመማር የሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡