የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ከሳሃይ ሶላር አሶሴሽን/Sahay Solar Association/ ጋር በመተባበር ከስዊዘርላንድ፣ ከጋሞና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ለተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተማሪዎች የፀሐይ ኃይልን ለመብራትና ለተለያየ አገልግሎት መጠቀም በሚያስችሉ ዘዴዎች /Photovoltaic Technology/ ዙሪያ ከጥር  30 - የካቲት 9/2015 ዓ/ም  ለተከታታይ 9 ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በ2015 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቅበላ ቀን የካቲት 22/2015 ዓ/ም፣ የምዝገባ ቀን የካቲት 23 እና 24 ቀን 2015 ዓ.ም ፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ስለሆነም ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩኒቨርሲቲው በሚትመጡበት ጊዜ፡-

 የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ በሚገኘው ሻማ ጎማ፣ ቀርጴ እና በሌ ቀርጴ መንደሮች ላይ በ1.9 ሚሊየን ብር ያስገነባውን የሻማ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የካቲት 12/2015 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ ከፕሮጀክት ሥራው 400 ሺህ ብር ወጪ የተሸፈነው ማኅበረሰቡ በጉልበቱ ባበረከተው አስተዋፅዖ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

Arba Minch University in collaboration with Deutsche Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit (GIZ), the main German Development Agency, hosted Inception and Promotion Workshop on “Women in Agriculture and Rural Livelihoods” on February 14, 2023. Click here to see more pictures.

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ‹‹GIZ›› ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ‹‹Women in Agriculture and Rural Livelihoods›› በሚል ርዕስ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎችና መምህራን በተገኙበት የካቲት 6/2015 ዓ/ም ወርክሾፕ አካሂዷል፡፡ በወርክሾፑ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡