በ2014 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቅበላ ቀን የካቲት 29/2015 ዓ/ም፣ የምዝገባ ቀን የካቲት 30 እና መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡ ስለሆነም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-   

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ‹‹የ21ው ክፍለ ዘመን በአፍሪካ የኢትዮጵያ ስትራቴጂ/Ethiopia’s Africa Strategy for Twenty-first Century›› በሚል ርዕስ የፖሊሲ የምክክር መድረክ የካቲት 17/2015 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕርነርሽፕ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት  ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኢንተርፕርነርሽፕ ሥልጠና በ25/06/2015 ዓ/ም አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም በግቢ ቆይታችሁ ከዚህ በፊት የኢንተርፕርነርሽፕ ሥልጠና ያልወሰዳችሁ ብቻ እና ለመውሰድ ፍላጎቱ ያላችሁ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከ2፡30 ጀምሮ በመገኘት ሥልጠናውን እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡