የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ረንረስ /RUNRES/ ፕሮጀክት ከ‹‹International Institute of Tropical Agriculture››፣  ‹‹University of Kwazulu-Natal››፣ ‹‹ETH-Zurich›› እና ከስዊዘርላንድ ልማት ተራድዖ ድርጅት (SDC)  ጋር  በመተባበር ከተማና ገጠርን በንጥረ ነገር ማስተሳሰር ላይ በሚሠራው ፕሮጀክት የ4ዓመት የፕሮጀክት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የምክክር ወርክሾፕ ከየካቲት 6-10/2015 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ፓራዳይዝ ሎጅ አካሂዷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከጋሞና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ከጀርመኑ ሰሃይ ሶላር ማኅበር ጋር ለቀጣይ ሦስት ዓመታት በታዳሽ ኃይል ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የካቲት 1/2015 ዓ/ም ተፈራርሟል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Arba Minch University, Sahay Solar Association, Gamo and Gofa Zonal Administrations have signed a Memorandum of Understanding for the next three years to install off-grid solar systems for off-grid electrification, on February 8, 2023. see more photos

ከየካቲት 6-8/2015 ዓ.ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጄዲሲ ኢትዮጵያ (JDC Ethiopia) ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በተፈጥሮ የጀርባ ጉብጠት (kyphosis)፣ ዝንፈት (Scoliosis) እና ጥመት ላለባቸው ታማሚዎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ስለሚሰጥ አርባ ምንጭ እና አካባቢው የምትገኙና ሕክምናውን የምትፈልጉ ታማሚዎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ያሳውቃል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ እና የምርምር ዳይሬክቶሬቶች በመተባበር ለጀማሪ ሴት መምህራን ‹‹Basic of Research, Statistical Tools for Data Analysis and Interpretation, Manuscript Writing and the Tricks of the Publishing›› በሚል ርዕስ የምርምር ክሂሎት ማዳበሪያ ሥልጠና ከጥር 23-24/2015 ዓ/ም ሰጥተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡