Arba Minch University held a kick-off meeting on July 22, 2023 to officially launch a 2.3 million ETB collaborative Project with the theme of “Production, Popularization, and Commercialization of Value added Enset-Based Food Products through the Adoption of Proven Processing -Technologies". Click here to see more pictures.

መምህር ሀብታሙ ሻቴ ከአባታቸው አቶ ሻቴ ዮሻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ባዩሽ በቀለ ታኅሣሥ 19/1972 ዓ/ም በቀድሞው ጋሞ ጎፋ አውራጃ ካምባ ወረዳ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በካምባ ባዮ 1 ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የ2 ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2 ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡

አርባ ምጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ስለፈተና አሰጣጥና በግቢ ውስጥ ስለሚኖራቸው ቆይታ ዛሬ ሐምሌ 24/2015 ዓ/ም ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በስድስቱም ካምፓሶቹ 6,546 ወንድ እና 4,857 ሴት በድምሩ 11,403 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር መርሃ ግብር መሠረት ፈተናውን ከሐምሌ 25/2015 ዓ/ም ጀምሮ የሚወስዱ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ12 ክፍል ሀገር አቀፍ የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ላይ ለቆዩ የፈተና አስፈጻሚዎች የአርባ ምንጭ አዞ እርባታ ማዕከልን እንዲጎበኙ በማመቻቸት ሐምሌ 22/2015 ዓ/ም ሽኝት አድርጓል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ተቋማት በሚቀጠሩበት ወይም ተቀጥረው እየሠሩ ባሉበት ጊዜ የሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ይጣራልን ጥያቄዎችን እየተቀበለ የትምህርት ማስረጃ አጣርቶ በማረጋገጥ በተከታታይ ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡