የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከ4ቱ ፋከልቲዎችና ከውሃ ምርምር ማዕከል ለተወጣጡ መምህራን ‹‹Basic Python for Environmental Data Processing›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 29 -ኅዳር 10/2015 ዓ/ም ድረስ የቆየ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ እና በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የምርምር ማስ/ጽ/ቤቶች አማካኝነት 85 የምርምር  ንድፈ ሃሳቦች ቀርበው  ከኅዳር 9-10/2015 ዓ/ም ተገምግመዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ3 ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ዕጩ ዶ/ር ስንታየሁ አሰፋ ‹‹DRIVERS AND IMPEDIMENTS OF EXPORT PERFORMANCE፡ EVIDENCE FROM TEXTILE AND GARMENT ENTERPRISES IN ETHIOPIA››  በሚል ርዕስ የሠሩትን የምርምር ሥራ ኅዳር 7/2015 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርበው ተገምግሟል፡፡  የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል ከጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ጋርና ከደረጃ ዶት ኮም/Dereja.Com Academy/  ከተባለ የግል ድርጅት ጋር በመተባባር ለአርባ ምንጭ ከተማ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ስለደረጃ ዶት ኮም አካዳሚ አክስለሬተር ፕሮግራም/Dereja.Com Academy Accelerator Program/ ሥልጠና ከኅዳር 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ወራት  እየሰጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስ/ጽ/ቤት እና የዩኒቨርሲቲው ባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን እና ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ባህል፣ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ እንዲሁም ከጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ‹‹የሙዚየም አደረጃጀት፣ አገልግሎት አሠጣጥና ተደራሽነት›› በሚል መሪ ቃል በደቡብ ክልል ካሉ ዞኖች ለተወጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከኅዳር 5-6/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡