- Details
የእናቶችንና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል በሚተገበረው ‹‹AMU-IUC›› ፕሮጀክት III ሥር ከሚከናወኑ ምርምሮች አንዱ የሆነውንና በጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ በነፍሰጡር እናቶችና ሕፃናት ጤና ሁኔታ ላይ በቪዲዮ የተመሠረተ የጤና ትምህርት የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለማወቅ የተደረገውን የሙከራ ጥናት ውጤት ለማኅበረሰቡ ለማስተዋወቅ ጥር 04/2016 ዓ/ም በጊዶሌ ከተማ ወርክሾፕ ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በቪዲዮ የተመሠረተ የጤና ትምህርት በእናቶችና ጨቅላ ሕፃናት ጤና ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በጥናት ተገለጸ
- Details
በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በግል የማካካሻ ትምህርት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 6/2016 ዓ.ም፣ የትምህርት ክፍያ የምትከፍሉት ከጥር 6 - 7/2015 ዓ.ም እና ትምህርት የሚጀመረው ጥር 8/2016 ዓ.ም ስለሆነ በግል ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ትምህርት እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡
- Details
እንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የ''McGee Group'' ባልደረባ የሆኑት አቶ ሌም ብርሃኑ እና ሚስ ቤላ ቨርመንት/Ms Bella Vermunt/ በራሳቸው ተነሳሽነት ያሰባሰቧቸውንና ለአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሚያገለግሉ 100 የምኅንድስና ሳይንስ ዘርፍ መጽሐፎችን በስጦታ አበርክተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: እንግሊዝ ሀገር የሚገኘው “McGee Group” ባልደረቦች በግል ተነሳሽነት ለቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 100 መጽሐፎችን አበረከቱ
- Details
በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ባለማምጣታችሁ ምክንያት የማካካሻ ትምህርት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንድትወስዱ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም ይሆናል፡፡
Read more: የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ
- Details
ጥር 2/2016 ዓ/ም ሊከበር የነበረው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ቀን በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ወደ ጥር 6/2016 የተዛወረ በመሆኑ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ይህንን በመረዳት በዕለቱ ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ ከዚህ ቀደም በተጠቀሰው የስብሰባ አዳራሽ ተገኝታችሁ ተሳታፊ እንድትሆኑ ከይቅርታ ጋር ያሳውቃል፡፡