እንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የ''McGee Group'' ባልደረባ የሆኑት አቶ ሌም ብርሃኑ እና ሚስ ቤላ ቨርመንት/Ms Bella Vermunt/ በራሳቸው ተነሳሽነት ያሰባሰቧቸውንና ለአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሚያገለግሉ 100 የምኅንድስና ሳይንስ ዘርፍ መጽሐፎችን በስጦታ አበርክተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ባለማምጣታችሁ ምክንያት የማካካሻ ትምህርት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንድትወስዱ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም ይሆናል፡፡

ጥር 2/2016 ዓ/ም ሊከበር የነበረው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ቀን በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ወደ ጥር 6/2016 የተዛወረ በመሆኑ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ይህንን በመረዳት በዕለቱ ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ ከዚህ ቀደም በተጠቀሰው የስብሰባ አዳራሽ ተገኝታችሁ ተሳታፊ እንድትሆኑ ከይቅርታ ጋር ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ በከፍተኛ ትምህርት የከፍተኛ አመራር ዝግጅት፣ ምልመላና ስምሪት ሥርዓት ማስተግበሪያ መመሪያ መሠረት ለሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ለመመደብ ባካሄደው ውድድር ከቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች መካከል ዶ/ር ደስታ ጋልቻን የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ሆነው እንዲያገለግሉ ከጥር 01/2016 ዓ/ም ጀምሮ ሾሟል፡፡

አርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ‹‹Emerging Digital Technologies for Improved Aquatic Ecosystem Services›› በሚል ርእስ ከስዊድን ሀገር ማልሞ ዩኒቨርሲቲ (Malmo University) ከመጡት ዶ/ር ፍሥሃ መኩሪያ ጋር ታኅሣሥ 25/2016 ዓ/ም   ሴሚናር አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ