- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ከፍተኛ የእንሰት አምራች በሆነው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያውን የእንሰት መፋቂያና ማብላያ የሙከራ ማዕከል /Enset Processing Pilot Plant/ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ አቋቁመው ታኅሣሥ 12/2016 ዓ/ም በይፋ ሥራ አስጀምረዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያው ዘመናዊ የእንሰት ማቀነባበሪያ የሙከራ ማዕከል ተቋቁሞ ሥራ ጀመረ
- Details
Arba Minch University (AMU) in collaboration with British Council hosted Ethiopian English Language Professionals’ Association/EELPA/ - South Chapter launching event in AMU on 23rd December, 2023. Click here to see more photos.
- Details
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማኅበር ጋር በመተባበር እንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ‹‹MCGee Group›› በመጡ የግንባታ ዘርፍ ነባር ባለሙያዎች አማካኝነት ለቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን፣ ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ለሚማሩ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል በግንባታ ዘርፍ ለሚሠሩ ባለሙያዎች ‹‹Risk Management for Construction Projects - A practical Insight›› በሚል ርእስ ከታኅሣሥ 11-12/2016 ዓ/ም ወርክሾፕ አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንደስትሪ አንቀሳቃሾች በምግብ ደኅንነት አስተዳደር ሥርዓት (FSMS:ISO 22000፡2018) ዙሪያ ታኅሣሥ 08/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
የዩኒቨርሲቲው የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ የእንስሳት መኖ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እና የአፈር ለምነትን መጠበቅ ላይ የሚሠራ የምርምር ሜጋ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ታኅሣሥ 09/2016 ዓ/ም በገረሴ ከተማ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የ1.6 ሚሊዮን ብር የምርምር ሜጋ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ