Collaborating with the Ethiopian Diaspora Taskforce, an interesting online training on Grant Proposal Writing is planned for all AMU academic staff and PhD candidates. The training will be offered by Prof Tesfaye B. Mersha (USA) who has a good record of winning grants as well as reviewing grant proposals. It is strongly recommended for all AMU staff members and PhD students to attend the training. Click here to see more Pictures.

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ትምህርት ክፍል በባዮቴክኖሎጂ ትምህርት ፕሮግራም ላለፉት አምስት ዓመታት የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ብርሃኑ ገመዳ የምርምር ሥራውን መጋቢት 22/2015 ዓ/ም የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ፎቶውን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የኢትዮጵያ ሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር በየዓመቱ የብሩህ ኢትዮጵያ ዓመታዊ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ያካሂዳል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለ2015 ዓ/ም ውድድር ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ሃሳብ ያላችሁ ተማሪዎች እንድትሳተፉ እንዲደረግ ባሳወቀው መሠረት የቢዝነስ ሃሳብ ያላችሁ ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው የመመዝገቢያ ሊንክና የቴሌግራም ግሩፕ በፍጥነት እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ- ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት በ2015 የትምህርት ዘመን አዲስ ለገቡ ተማሪዎች በዋናው ግቢ እና ጫሞ ካምፓስ በሥነ-ምግባር ምንነት፣ መሠረታዊ መርሆዎች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ሥነ-ምግባር መመሪያና በሙስና ወንጀል ዙሪያ መጋቢት 23/2015 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶ ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡