የአርባ ምንጭ ከተማ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ከ‹‹UNDP›› ፕሮግራም ጋር በመተባበር ከከተማዋ የተወጣጡ ወጣቶች ባቀረቡት የሥራ ፈጠራ ላይ ሰኔ 23/2014 ዓ/ም ውድድር አካሂዷል፡፡ ውድድሩ በጽንሰ ሃሳብ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን የተወሰኑት በተግባር የተደገፉ ማሳያዎችን አቅርበዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ተመራቂ ተማሪዎች በሥነ-ምግባርና በሙስና ወንጀሎች ዙሪያ ሰኔ 20/2014 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

አርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ‹‹Ethio Jobs›› አጋር ድርጅት ከሆነው ‹‹Derja.com›› ጋር በመተባበር ለ2014 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች ‹‹Self Discovery››፣ ‹‹Building Self Image››፣ ‹‹Communication at the Work Place››፣ ‹‹Analytical Thinking››› በሚሉና ሌሎችም ርዕሶች ዙሪያ ከሰኔ 17-21/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለጂኦግራፊና አካባቢያዊ ጥናት ት/ክፍል መምህር ዶ/ር አበራ ኡንቻ እና ለውሃ አቅርቦትና አካባቢ ምኅንድስና ፋከልቲ መምህር ዶ/ር አክበር ጩፎ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን በቅድመ ምረቃ 193 እና በ2ኛ ዲግሪ 6 በድምሩ 199 ተማሪዎችን ሰኔ 26/2014 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 89ኙ ሴቶች ናቸው፡፡