የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዘንድሮው ዓመት የሚያስመርቃቸው የሕክምና ዶክተሮች ሀገር አቀፉን የመውጫ ፈተና መቶ በመቶ ማለፍ ችለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ በተገኘው ውጤት የተሰማቸውን ደስታ በዩኒቨርሲቲው ስም እየገለጹ ለተመራቂ የሕክምና ዶክተሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ሦስት ፕሮጀክቶች የደረሱበት ደረጃ የመጀመሪያ ዙር ግምገማ የካቲት 08/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የጋሞ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ መምሪያ የጫሞ ሐይቅ ረግረጋማ ስፍራን/Buffer Zone/ መልሶ ለማልማትና ለመጠበቅ የሚያስችል 1.65 ሄክታር ተጨማሪ መሬት ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ /AMU-IUC/፣ ጋንታ አባ እና ባይራ ለተሰኙ ማኅበራት የካቲት 08/2016 ዓ/ም አስረክቧል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሠለጠናቸውን የሕክምና ዶክተሮች ለ9 ጊዜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ በዋናው ግቢ መግቢያ በር አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ ከጧቱ 2፡00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኮንሶ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ጋር በመተባበር በሰብአዊ መብት አያያዝና አጠባበቅ እንዲሁም በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ በኮንሶ ዞን ለሚገኙ 250 የፖሊስ አባላት ከየካቲት 6-9/2016 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ