የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሠረት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአማካሪ ምክር ቤት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በጋሞ ዞን ጨንቻ ወረዳ ዶርዜ ቀበሌ የቴክኒክና ሙያ እና የዩኒቨርሲቲ ትምህርት አጠናቀው ሥራ ላጡና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ እማወራ ሴቶች ከቀርከሃ ምርት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማምረትና መሸጥ የሚያስችል ሥልጠና ከጥቅምት 16/2013 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች መምህራን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በዋናዉ ግቢ አቅራቢያ ከሚገኙ ሦስት ቀበሌያት ለተወጣጡ 100 ተማሪዎች የመማሪያ ደብተርና እስክሪፕቶ ድጋፍ ጥቅምት 19/2013 ዓ.ም አድርጓል፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት መማር ማስተማርን ለማስቀጠል ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በቀረበው የመተዳደሪያ መመሪያ ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጥቅምት 20/2013 ዓ/ም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሥራን ለማስቀጠልና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የመተዳደሪያ መመሪያ መኖሩ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አመራር፣ መምህራን፣ አስተዳደር ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎች በግቢ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ አካላት መመሪያውን በአግባቡ ተፈፃሚ እንዲያደርጉ ዶ/ር ዳምጠው አሳስበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ለአርባ ምንጭ ዩነቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ተግባቦት አማራጮች ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 25 እና 26 ግቢ እንድትገቡ ከጥቅምት 03/2013 ዓ/ም ጀምሮ ያስተዋወቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በተፈጠረው አሁናዊ አገራዊ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ አከባቢዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር የተፈጠረ መሆኑን መገንዘብ ችለናል፡፡