የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማኅበር፣ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በመተባበር ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በሚያስችሉ አዳዲስ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከጥቅምት 30 - ኅዳር 04/2013 ዓ/ም የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡ አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው 2ኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡ አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው 2ኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የምርምርና ማኅበረሰብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት ጋር በመተባበር ከሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ፣ ከጤና ሳይንስ እና ከማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጆች የተወጣጡ መምህራን ባቀረቡት የምርምር ንደፈ ሃሳብ ላይ ኅዳር 04/2013 ዓ/ም ግምገማ አካሂዷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ IUC ፕሮጀክት ‹‹በደቡብ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ በዓባያና ጫሞ ተፋሰስ የመሬት መራቆትን መቀነስ ለዘላቂ የመሬት አጠቃቀም›› በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 20/ 2013 ዓ/ም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ዓውደ ጥናት አካሂዷል፡፡