በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ በወዜ ቀበሌ በሚገኘው አርባ ምንጭ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የተከናወነው የአንድ ብሎክ ሕንፃ የማስፋፊያ ክፍሎች ግንባታ ተጠናቆ ኅዳር 19 /2013 ዓ/ም ተመርቋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በውስጣዊና ውጫዊ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ኅዳር 11 /2013 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡

በኮንሶ ዞንና አካባቢው በተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሚገኙ ወገኖች ዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ኅዳር 15/2013 ዓ/ም ድጋፍ አድርጓል፡፡ በዕለቱ 156 ፍራሽ፣ 28 ካርቶን ሳሙና እና 5 እሽግ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከተፈናቃዮቹ በቀረበው ጥያቄ መሠረትም የውሃ አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት እየተሰጣቸው ነው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሕግ በማስከበር ሂደት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸውና ደም ለሚያስፈልጋቸው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት አጋርነታቸውን ለመግለጽ ኅዳር 14/2013 ዓ.ም በሁሉም ካምፓሶች ደም የመለገስ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ላላቸው የሥነ-ልቦና፣ ጋይዳንስና ካውንስሊግ እና የዜሮ ፕላን ባለሙያዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሠራተኞች እንዲሁም የተማሪዎች መኝታ ቤት፣ የምግብ አገልግሎት፣ የሰላም ፎረምና የደኅንነትና ጥበቃ አስተባባሪዎች የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎት አሰጣጥንን በተመለከተ ከኅዳር 10-11/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ