አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ጂኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በጂኦ ስፓሻል ትምህርትና ሥልጠና፣ ምርምር፣ ዕድገት እንዲሁም መረጃ ልውውጥ ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለ7 ወራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የቅድመ ምረቃ ትምህርት ለማስጀመር በመማር ማስተማሩ ዘርፍ አስፋላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ ገልፀዋል፡፡

ላለፉት ሦስት ዓመታት እየጣለ ባለው ዝናብ አማካኝነት እየገባ ባለው ከፍተኛ ደለል ምክንያት የዓባያና ጫሞ ሐይቆች ከመጠን በላይ መሙላታቸውና ከብዙ ዓመታት በኋላ ሐይቆቹ ዳግም መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡ ላለፉት 45 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው ጫሞ በሰገን በኩል የሚያደርገው ፍሰትም ጥቅምት 16/2013 ዓ/ም ዳግም ጀምሯል፡፡

የ2013 የትምህርት ዘመን፡-

1. የምዝገባ ቀናት - ከጥቅምት 18-20/2013 ዓ.ም

2. የምዝገባ ቦታ - በካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች

3. ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ጥቅምት 23/2013 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

በ2012 ዓ/ም በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት በ2013 የትምህርት ዘመን እንዲቀጥል መንግሥት በወሰነው መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎችን ከጥቅም 25 – 26/2013 ዓ/ም የመልሶ ቅበላ መርሃ ግብር ያካሂዳል፡፡