የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማስተባበሪያ ማዕከል ‹‹አፍሪካን - ኢትዮጵያን ከምዕራባዊያን ተጽዕኖ እንዴት ነፃ እናድርጋት?›› በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ ሲምፖዚየም የካቲት 24/2014 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው በትምህርት ጥራት ዙሪያ ዋና ዋና ችግሮችን ለይቶ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የካቲት 25/2014 ዓ/ም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ ተወካዮች በተገኙበት ባደረጉት ስብሳባ ገልጸዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግሥት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር 126ኛውን የዓድዋ ድል ክብረ በዓል ‹‹ዓድዋ ለኢትዮጵያዊያን ኅብረት ለአፍሪካዊያን የነፃነት ጮራ›› በሚል መሪ ቃል የካቲት 23/2014 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው በደማቅ ሁኔታ አክብሯል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፤ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡

ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተወጣጡ አካዳሚክ አመራር አካላትና መምህራን ‹‹Academic Program Audit››፣ ‹‹Academic Program Standardization›› እና ‹‹Academic Program Accreditation›› በሚሉ ይዘቶች በትምህርት ፕሮግራም ጥራትና አግባብነት ዙሪያ ከየካቲት 21-22/2014 ዓ/ም ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ