የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ጽ/ቤት እና ከምርምር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ኅዳር 20/2016 ዓ/ም በዶርዜ ሆሎኦና ላካ ቀበሌ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል እንዲሁም በአርሶ አደር ማሳ ላይ የሚገኙ የቢራ ገብስ ዝርያዎች የመስክ ምልከታና የዝርያ መረጣ አካሂዷል፡፡  ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በ2016 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ለመማር አመልክታችሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ቅበላ ፈተና (National Graduate Admission Test – NGAT) ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያመጣችሁና የተመዘገባችሁ አዲስ አመልካች ተማሪዎች ፡-

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ተማሪ የሆኑት መቅደላይት ፈቃደ፣ ሰላማዊት ይብዛው እና ሜላት ገ/መድኅን ከግንቦት 29-30/2023 በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ በተካሄደው አምሳለ ፍርድ ቤት ውድድር ከሐሮማያ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ባሕር ዳር እና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ጋር በመወዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ አሸናፊ ሆነው ለአህጉራዊ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው እንዲገኙ መመረጣቸው ይታወሳል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ‹‹መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!!›› በሚል መሪ ቃል 18ኛውን ሀገር አቀፍ የነጭ ሪባን ቀን ከኅዳር 16/2016 ዓ/ም ጀምሮ በማክበር ላይ ይገኛል፡፡ አከባበሩ እስከ ታኅሣሥ 1/2016 ዓ/ም የሚቆይ ሲሆን በሁሉም ካምፓሶች የሚገኙ ተማሪዎችንና የአስተዳደር ሠራተኞችን በማሳተፍ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት መንስኤና የሚያስከትለው ችግር ላይ አጠር ያለ ሥልጠና፣ ውይይት እንዲሁም የተለያዩ ሥነ ጽሑፎች በተማሪዎች እየቀረቡ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ