በኮንትራት ውል መሠረት በደብዳቤ የተስተናገዳችሁ የቀድሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2ና 3 ዲግሪ ተመራቂዎች የቀድሞ ደብዳቤ ወደ ሰርተፊኬት እንዲቀየርላችሁ የቀረበ ጥያቄ በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል ውሳኔ ማግኘቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሠረት የምረቃ ደብዳቤው ወደ ሰርተፊኬት እንዲቀይርላችሁ የምትፈልጉ በሙሉ በእጃችሁ የሚገኘውን የቀድሞ ደብዳቤ ኮፒ በመመለስ ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ (Temporary Certificate of Graduation) ከሰኞ ታኅሣሥ 15/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ወቅታዊውን የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ አስመልክቶ ‹‹የባሕር በር የልማት በር›› በሚል ርእስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ/ም የፓናል ውይይት አዘጋጅቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ምርምር ማዕከል ጨንቻ በሚገኘው ግርጫ የደጋ ፍራፍሬና አትክልት ምርምር ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘመናዊ የወተት ላሞች እርባታ ጣቢያ /Dairy Farm/ እያስገነባ ይገኛል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴርና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከወልቂጤ፣ ወራቤ፣ ዋቸሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጂንካ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ለመጡ የግዥና ንብረት እና የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎች፣ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች የሚመለከተቸው አካላት ሙስናን መከላከልና መቆጣጠርን አስመልክቶ ከታኅሣሥ 05 - 06/2016 ዓ/ም የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት”በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት የአስተዳደር ኃላፊዎችን ጨምሮ ርዕሰ መምህራን፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት ታኅሣሥ 05/2016 ዓ.ም በድምቀት ተከብሯል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡