- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ሰኔ 14/213 ዓ/ም ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መልስ በዋናው ግቢ የችግኝ ተከላ በማካሄድ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መልስ የችግኝ ተከላ አካሄዱ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ዕቅድና ፕላን መምሪያ፣ አየር ንብረትና አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ቴክኒክና ሙያ መምሪያ፣ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ ከተማ ልማት፣ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት፣ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ ጤና መምሪያ እና ጋሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ለተወጣጡ ባለሙያዎች በ‹‹GIS››፣ ‹‹GPS›› እና ሪሞት ሴንሲንግ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከሰኔ 7-11/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል:: ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ዩኒቨርሲቲው ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ ባለሙያዎች በ‹‹GIS››፣ ‹‹GPS›› እና ሪሞት ሴንሲንግ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ
- Details
የዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ማኅበረሰበሰ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከምራብ ዓባያና ከአርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ግንቦት 14/2013 ዓ/ም የተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ክሂሎት ማሻሻያ ዙሪያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሥልጠናው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፊደላት፣ ድምጽና ስያሜያቸው እንዲሁም ተነባቢና አናባቢ ድምጾች በቃላት ውስጥ ሲገቡ የሚያመጡትን ለውጥ ለተማሪዎቹ የሚያስተምሩበት ስነ-ዘዴ በስፋት ተዳሷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ክሂሎት ማሻሻያ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
የዩኒቨርሲቲው ስፖርት አካዳሚ ከፌዴራልና ከደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽኖች ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ወረዳዎችና አርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ የስፖርት ባለሙያዎችና የስፖርት መምህራን ከሰኔ 2-11/2013 ዓ/ም የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የ1ኛ ደረጃ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥራ ፈጠራ ልማት ማፍለቂያ ማዕከል ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዘርፍ ጽ /ቤት ጋር በመተባበር ለአርባ ምንጭ ከተማ ስራ አጥ ወጣቶች በመሠረታዊ ሥራ ፈጠራ ክሂሎት ላይ የሥራ ፈጠራ ማነቃቂያ ሥልጠና ሰኔ 11/2013 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው ውስጣዊ ተነሳሽነት እንዲፈጠር የማነቃቂያ ሃሳቦች፣ መሠረታዊ የሥራ ፈጠራ ክሂሎት፣ የቢዝነስ ዕቅድ አዘገጃጀት እና መልካም አጋጣሚዎችን ወደ ሥራ ፈጠራ ሃሳብ መቀየር በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለአርባ ምንጭ ከተማ ስራ አጥ ወጣቶች መሠረታዊ የሥራ ፈጠራ ክሂሎት ሥልጠና ተሰጠ