- Details
የሃይድሮሊክስና ውሃ ሀብት ምኅንድስና ፋከልቲ ከኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለመጡ መምህራን የቤተ-ሙከራ ዕቃዎች አያያዝ፣ አጠቃቀምና አስተዳደርን በተመለከተ ከሰኔ 07-11/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የሃይድሮሊክስና ውሃ ሀብት ምኅንድስና ፋከልቲ ከኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለመጡ መምህራን ሥልጠና ሰጠ
- Details
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ‹‹Biodiversity Conservation and Management›› የትምህርት ፕሮግራም በ3ኛ ዲግሪ ለማስመረቅ የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ አጠናቋል፡፡ ዕጩ ተመራቂ ዶ/ር ዘውድነህ ቶማስ ለምረቃ ብቁ የሚያደርገውን ጥናታዊ ጽሑፍ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በተገኙበት ሰኔ 21/2013 ዓ/ም አቅርቧል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
ዩኒቨርሲቲው ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ለድል ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አድርጓል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ድል ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በከተማው በሆስፒታል ደረጃ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልጸው ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን የሕክምና አገልግሎት ጫና የሚቀንስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቪርሲቲ ለድል ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ዓመታዊውን የምርምር ሥራዎች የመስክ ጉብኝት የኮሌጁ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች በተገኙበት ሰኔ 24/2013 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ