ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ የክረምት መርሃ-ግብር ተማሪዎች በሙለ

የ2014 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ምዝገባ ሐምሌ 4-5/2014 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት
በየካምፓሶቻችሁ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እየገለጽን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን
ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ እንዲሁም ይህ ማስታወቂያ የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን
የማይመለከት መሆኑን ያስታውቃል፡፡


የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የእንግሊዝ ተራድኦ ድርጅት (FCDO) ድጋፍ የሚያደርጉለት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስር የምርምር ውጤቶች ወደ ገበያ የሚገቡበት የገንዘብ ድጋፍ ውድድር ላይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊ ሆኗል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስር በሚገኙ ሚቲዎሮሎጂ እና ሀይድሮሎጂ ፋከልቲዎች በቀረቡ 2 የሦስተኛ ዲግሪና 1 የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ሰኔ 6/2014 ዓ/ም የውጭ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከሰኔ 4-5/2014 ዓ/ም በአዲስ ገቢ ተማሪዎች መካከል የእግር ኳስ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ምርምር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ግሽበት አስመልክቶ በተሠራ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ለት/ክፍሉ መምህራንና ለባለ ድርሻ አካላት ሰኔ 3/2014 ዓ/ም ትምህርታዊ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡