በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ሲታዩ የቆዩ የግድያ፣ የአስገድዶ መድፈር እና የአዳራሽ ወንበር ግዢ ክሶች የፍ/ቤት ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆኑ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር ተገልጿል፡፡

የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ለተማሪዎች አደረጃጀት፣ ለክበባት አስተባባሪዎችና ለሴት ተማሪዎች መኝታ አስተባባሪዎች ታኅሣሥ 23/2014 ዓ/ም የካምፓስ ሕይወት አማካሪነት/ Campus Life Mentorship/ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የልማት ሥራዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች እየተሠሩ ያሉ የአካባቢና ደን ጥበቃ ሥራዎች ያሉበት ነባራዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ታኅሣሥ 25/2014 ዓ/ም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ እየተሠሩ ያሉ የአካባቢና ደን ጥበቃ ሥራዎች፣ ያሉባቸው ችግሮችና የ2014 ዓ/ም የችግኝ ስርጭት ዕቅድ በውይይቱ ተነስተዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ማኅበረሰብ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (ገና) በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልጻል!!

መልካም ገና!!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከደቡብ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲና ከጋሞ ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሻራ ቀበሌ እንዲሁም በምዕራብ ዓባያ ወረዳ አንኮበርና ኤልባ ቀበሌያት የሚገነቡትን የባዮ ጋዝ ማብለያዎች ታኅሣሥ 22/2014 ዓ/ም የመስክ ምልከታ አካሂደዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ