የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ነባር ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 23-24/2014 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 29/2014 ዓ/ም ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና “Christian Aid” የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት በኢኖቬቲቭ እንሰት ፕሮጀክት የተሠሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንሰት አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ለማዳረስ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ ከድርጅቱ የመጡ የሥራ ኃላፊዎች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በመሆን ጥቅምት 9/2014 ዓ/ም በዶርዜና ግርጫ ምርምር ማዕከላት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በቅርቡም የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ወደ ተግባር እንደሚገባ ታውቋል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ 

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አውስትራሊያ ሀገር ከሚገኘው “Menzies School of Health Research” ከተሰኘ የጤና ምርምር ት/ቤት ጋር ‹‹Effectiveness of Novel Approaches to Radical Cure of Vivax Malaria with Tafenoquine and Primaquine›› በሚል ርዕስ 210 ሺህ ዶላር የተመደበለት ግራንድ የምርምር ፕሮጀክት ለማከናወን ጥቅምት 5/2014 ዓ/ም የመግባቢያ ስምምነት በቨርችዋል ተፈራርመዋል፡፡  

የዩኒቨርሲቲው ሁሉ አቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ከአርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ በኤችአይቪ/ኤድስ ለተጎዱና አቅም ለሌላቸው 200 ተማሪዎች ጥቅምት 2/2014 ዓ/ም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም 2ኛውን ዓለም አቀፍ የኦሞቲክ ቋንቋ ዓውደ ጥናት ከጥቅምት 01-02/2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ በዓውደ ጥናቱ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት በኦሞቲክ ቋንቋ ላይ የተሠሩ 17 ጥናቶች ቀርበው የቋንቋው ተናጋሪዎች ባሉበት ተገምግመዋል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ