- Details
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የ2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ዙር የምርምር ንድፈ ሃሳብ ግምገማ መስከረም 14/2014 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2014 ዓ/ም የምርምር ንድፈ ሃሳብ ተገመገመ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ፣ ምዕራብ ዓባያ፣ ቁጫ፣ ጨንቻና ገረሴ ወረዳዎች ለማኅበረሰቡ የባዮ-ጋዝ ግንባታ ለማካሄድ መስከረም 4/2014 ዓ/ም የውል ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ በዚህም መሠረት ከዩኒቨርሲቲው ለሥራ ማስፈፀሚያ 1,875,000 (አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሰባ አምስት ሺህ) ብር እና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ 4,054,115 (አራት ሚሊየን ሃምሳ አራት ሺህ አንድ መቶ አሥራ አምስት) ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የባዮ-ጋዝ ግንባታ ለማካሄድ ስምምነት ተፈራረመ
- Details
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በዋናው ግቢ ለተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት 600 ወንድ ተማሪዎች መስከረም 14/2014 ዓ.ም የማነቃቂያና የልምድ ልውውጥ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ተዘጋጀ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በድኅረ ምረቃ ት/ቤት የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ የነበሩት እጩ ዶ/ር ዓለማየሁ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ በነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክና በGIZ ትብብር በጫሞ ሐይቅ ላይ ለዓሳ መራቢያነት በተከለለው 100 ሄክታር የመራቢያ ቦታ ምክንያት በሐይቁ ላይ ጠፍተው የነበሩ እንደ <<Labeobarbus bynni>> እና ከዚህ ቀደም ታይተው የማይታወቁ <<Shilbe intermedius>> የተሰኙ ሁለት የዓሳ ዝርያዎች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ