የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች በሚገኙ 13 ቀበሌያት ንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የፈፀሙትን አሰቃቂ ግድያና ዝርፍያ በማውገዝ ሚያዝያ 17/2008 ዓ/ም የህሊና ፀሎትና የጧፍ ማብራት ሥነ-ሥርዓት አከናውኗል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

 

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ድርጊቱ በእጅጉ የሚያሳዝን፣ የበርካታ ንፁሐን  ዜጎችን ህይወት የቀጠፈና ንብረታቸውን ያዘረፈ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ላይ የተቃጣ የጥፋት ዘመቻ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ አክለውም ህዝቦቿ ተቻችለውና ተፋቅረው የሚኖሩባት የአንድነት መድረክ ሆና ለዘመናት የቆየችው ሀገራችን ኢትዮጵያ የወቅቱን የጋራ ጠላት ድህነትና ኋላቀርነትን ለመቅረፍ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቁርጠኝነት የተነሳች ሲሆን ለዚህም የተማረ የሰው ኃይል በማምረት የሀገሪቱን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተስፋ ተጥሎባቸዋል ብለዋል፡፡ ከተቋማቱ አንዱ የሆነው ዩኒቨርሲቲያችን የሀገሪቱን ህዳሴ ለማፋጠን በሚተጋበት በዚህ ወቅት ይህን መሰል ኢ-ሰብአዊና ፀረ-ልማት ጥቃት መከሰቱ በእጅጉ የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ ነው፡፡

ፕሬዝደንቱ በክስተቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በዩኒቨርሲቲው ስም ገልጸው በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችና ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሚወሰዱ እርምጃዎችና የሰላም ማስከበር ሂደት በሙሉ ከህዝቡና ከመንግሥት ጎን እንደሚቆምም አረጋግጠዋል፡፡

የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንት ተማሪ ዮርዳኖስ መኩሪያው ድርጊቱ ኢ-ሰብዓዊና መላውን የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ያስቆጣ አሳዛኝ ክስተት መሆኑን ገልፆ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን በመሆን ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት ያወግዛሉ ብሏል፡፡

የጋምቤላ ተወላጅ የሆነው የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ዴቪድ ሮው የሀዘን መግለጫ ሥነ-ሥርዓቱን