አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አንድ ኮሌጅ፣ ዘጠኝ ት/ክፍሎች/ፋከልቲዎች፣ ሁለት ተመራማሪዎች እና ሦስት የአስተዳደር ሠራተኞች ዕውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ጥቅምት 27/2016 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ዙር ኅዳር 5 እና 6 ቀን 2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በበይነ መረብ ይሰጣል፡፡ ይህ የመግቢያ ፈተና በ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በማንኛውም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድኅረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ የሆኑ አመልካቾችን ለመለየት አልሞ የሚሰጥ ሲሆን አዲስና ፈተናውን ደግመው የሚወስዱ አመልካቾች እስከ ኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ምሽቱ 12፡00/አሥራ ሁለት ሰዓት/ ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖርታልን (https://portal.aau.edu.et) ተጠቅመውና በቴሌብር 1000.00 ብር ከፍለው መመዝገብ ይችላሉ፡፡

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial / ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉትን ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በግል ከፍሎ ለመማር የሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ ‹‹Geography and Environmental Studies›› ት/ክፍል በ‹‹Environment and Natural Resource Management›› የትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ገነሻ ማዳ ኅዳር 03/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የ3 ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ መግቢያ አካባቢ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያቀርባል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት የ2016 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት የወላጅ ጉባኤ ጥቅምት 24/2016 ዓ/ም ያካሄደ ሲሆን በ2015 የትምህርት ዘመን በ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አምስት የት/ቤቱ ተማሪዎች ስጦታ አበርክቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡