የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ት/ክፍል ተማሪዎች 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ኅዳር 27/2017 ዓ/ም የጎዳና ላይ የጽዳት ዘመቻ አከናውነዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የዝግጅቱ አስተባባሪ የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ት/ክፍል ኃላፊ ዳመነ ቦጋለ የበዓሉ መከበር ከቱሪዝም የልማት ሥራዎች ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው መሆኑን ጠቅሰው ጎዳናዎችን ለጎብኚዎችና ለበዓሉ ተሳታፊዎች ጽዱና ምቹ ለማድረግ በማለም የጽዳት ዘመቻው መካሄዱን ገልጸዋል፡፡
19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ‹‹ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በአርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይከበራል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት